በአስተዳደራችን ካሉ የገጠር ቀበሌዎች በሀሎ ቡሳ እና ለገኦዳ ሚርጋ ለበርካታ አመታት የመልካም አስተዳደር ችግር በሚል ሲነሳ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር እንዲሁም በውሃ እጦት ሲነሱ የነበሩ የውሃ ወለድ በሽታዎች ለመከላከል በሚል የተጀመረው የሀሎቡሳለገኦዳ ሚርጋ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚችልበት አቅም ላይ መድረሱን መመልከት ተችሏል።
በጉብኝቱ ሂደት አንዳንድ የአከባቢው ነዎሪዎች እንደገለፁት ለበርካታ አመታት አከባቢው ምንም አይነት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የሌለበት አካባቢ እንደነበረና ህብረተሰቡም ለውጥ ወለድ እና ሌሎች ተዛማች በሽታዎች ሲጋለጥ እንደነበረ ፣ የትምህርት እና የጤና ተቋማትም ከውሃ ችግር የተነሳ አገልግሎት መስጠት የማይችሉበት ደረጃ ደርሰው እንደነበረ ጠቁመዋል። አሁን ግን መንግስት ችግር እጃችንን ተረድቶ በደረገው ከፍተኛ ጥረት ይህ ችግራችን ሊቀረፍ ከዳር መድረሱ በአይናቸው መመልከት እንደቻሉ ነዋሪዎቹ ጨምረው ገልጸዋል ።
በመስክ ምልከታው የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ የግብርና ውሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ኤልያስ አልይ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።


