የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሀ ፣ መስኖ ፣ ቆላማ አካባቢ እና የአካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ በድሬዳዋ አስተዳደር ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል

    በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሀ ፣ መስኖ ፣ ቆላማ አካባቢ እና የአካባቢ ጥበቃ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አህመድ እንዲሁም የቋሚ ኮሚቴው አባላት በድሬዳዋ አስተዳደር ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጉብኝቱን አስመልክቶ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አህመድ በሰጡት መግለጫ ቋሚ ኮሚቴው በተሰጠው ሃላፊነት መሰረት የሚሰራቸውን የክትትል ፣ ቁጥጥር እና የድጋፍ ስራዎች በክልል ደረጃ የሚገኙበትን ደረጃ ለመመልከትና ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምልከታ ለማድረግ አላማ ያደረገ ጉብኝት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
    በዛሬው እለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አመራሮች እና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች በተገኙበት ቋሚ ኮሚቴው ክትትልና ድጋፍ ከሚያደርግባቸው ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ተቋማቱ እያካናወኑ በሚገኙት ስራዎች ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡