በአሰተዳደራችን በ15 ቀን አንዴ የሚካሄደዉ ከተማ አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ዛሬ ለ33ኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን በቀበሌ 01አሰተዳደር ከ መልካ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚወሰደዉ አሰፓልት መንገድ የአሰተዳደራችን ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃርን ጨምሮ በ ካቢኔ ደረጃ ያሉ ከፍተኛ አመራር እሰከ ቀበሌ አመራር ደረጃ ያሉ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በተለያዩ በጎ ተግባር ላይ የሚሳተፉ የወጣት ማኀበራት አባላት በተገኙበት ለሁለት ሰአት የጽዳት ዘመቻ ተከናዉኑዋል ።
በጽዳት ዘመቻዉ ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎችን ለሰሩት በጎ ተግባር ምሰጋና ያቀረቡት የድሬዳዋ አሰተዳደር የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የ አንድ ከተማ ጽዳትና ዉበት ከ ከተማ እድገት ባሻገር የ መኀበረሰቡን የስልጣኔ ደረጃ የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዉ ድሬዳዋን ውብ እና ጽዱ ከተማ ለማድረግ የተጀመረዉ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ቁሻሻን የሚጸየፍ መህበረሰብ የማፍራት ስራ የሁላችንም ኃላፊነት ነዉ ብለዋል።
ሃላፊዉ አክለዉም ወጣቶች አሁን የጀመሩትን የበጎ አገልግሎት ሰራ በዚህ ክረምት ወራት በይበልጥ በማጠናከር ደጋፊ ለሌላቸዉ አዘዉንቶች ቤት የማደሰ፣የችግኝ ተከለና በመሳሰሉት የበጎ አገልግሎት ስራዎች ላይ በየ ደረጃዉ በሚወርድላቸዉ መረሃ ግብር ላይ ከበፊቱ በበለጠ ተሳትፎአቸዉን በማሳደግ ለከተማቸዉ ያላቸዉን ፍቅር በተግባር የሚያረጋግጡበት ወቅት ነዉ ብለዋል።


