የተገኙ ተቋማዊ ለውጦችን በማስቀጠል ለድሬደዋ ፍፁም ሰላማዊነት ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ::

    ኮሚሽነር አለሙ መግራን ጨምሮ የማእረግ እድገትና በተሻለ የአመራር ብቃት ተሸላሚ ለሆኑ ስትራቴጂክ አመራሮች የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም ተካሂዷል::
    የኢ/ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባሳለፍነው ግንቦት ወር የስትራቴጂክ አመራር የመአረግ እድገትና እንዲሁም በተሰጠ የአመራር ብቃት የተሻለ የመሪነት ሚና ለነበራቸው አመራሮች የሜዴይና ሌሎች እውቅናና ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ይህንንም በማስመልከት ነው በመድረኩ የመአረግ እድገት ላገኙና ሽልማት ለተበረከተላቸው የድ/ዳ ፖሊስ አመራሮች በትላንትናው እለት በድ/ዳ ፖሊስ የምስጋናና የእንኳን ደስ ያላችሁ መርሀ ግብር የተካሄደው::
    በመድረኩ በክብር እንግድነት የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለተሻለሚዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ካላ በሃላ እንደ ድሬደዋ ፖሊስ በተቋማዊ ሪፎርም ያገኛቸውን የስራ ውጤታማነት ይበልጥ በማስቀጠል በቀጣይም ለከተማው ፍፁም ሰላማዊነት ይበልጥ በህብረትና በአንድነት መስራት ይገባል ብለዋል::
    በም/ከንቲባ መአረግ የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው በድሬደዋ ከሶስትና አራት አመታት በፊት ተከስቶ የነበረውን ግጭት ሁከትና ረብሻን በመቆጣጠርና ወደ ቀደመ ሰላሟ በመመለስ ረገድ የተሰሩ ስራዎች እጅግ ውጤታማ እንደነበሩ ገልፀው ::ይህን በመምራትና በመፈፀም እረገድ አመራርና አባሉ ለነበረው ሚናና ድርሻ ይህ አይነቱ ሽልማትና እውቅና ይገባል እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል::
    በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትላንት ምሽቱን በተካሄደው መርሀ ግብር የም/ኮሚሽነርነት መአረግና የመጀመሪያ ደረጃ የወርቅ ሜዴይ ላገኙት ኮሚሽነር አለሙመግራ እንዲሁም ወደ ም/ኮሚሽነርነትና ረ/ኮሚሽነርነት ለተሻገሩት ም/ኮሚሽነር ታምራት እራርሳና ረ/ኮሚሽነር ጌታሁን አበራ ብሎም በተሻለ የአመራር ብቃት ተሸላሚ ለሆኑት ሶስቱ የዘርፍ ሃላፊ ም/ኮሚነሮች
    የመታሰቢያ ሶጦታ ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል ሲል የዘገበዉ ድሬ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነዉ