የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለመንግስት እና ግል ጤና ተቋማት ነው ምስጋናና አውቅናውን የሰጠው::
የተጎዱ የሰራዊት አባላትን የህክምና አገልግሎት የሰጡና በአፋር ክልል በጦርነቱ የወደሙ ጤና ተቋማትን ለማቋቋም ግብአት በማሰባሰብ ለተሳተፉ አካላት ምስጋና ለማቅረብ ፕሮግራሙ መዘጋጀቱን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ተናግረዋል::
የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደረጃ ፀጋዬ በበኩላቸው በተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ የጤና ባለሙያዎች እና ጤና ተቋማት ሚና ትልቅ እንደነበር ያሰታወሱት ኃላፊዉ ላደረጉት ድጋፍ በማመሰገን በቀጣይም ሀገራቸዉ በምትፋልጋቸዉ ወቅት ሁሉ ድጋፋቸው በሁሉም መስክ ተጠናክሮ እንደሚቀል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
መረጃዉን ያደረሰን DMMA ነዉ


