#አረንጓዴ_ዐሻራችን – ለትውልዳችን❗ 4ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። እኛ ድሬዎች ደግሞ የተፈጥሮ አደጋ ብዙ ዋጋ አስከፍሎናልና፤ የአረንጓዴ ልማትን ጥቅም ከማንም በላይ እናውቀዋለን። ስለሆነም መላው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች፤ በቀጣይ ጊዜያት በተባበረ ክንድ ችግኞችን በመትከል፤ ለአረንጓዴ ዐሻራ ግብ ስኬት ኃላፊነታችሁን ከወዲሁ ለመወጣት እንድትዘጋጁ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ከድር ጁሃር የድሬዳዋ አሰተዳደር ከንቲባ


