“አረንጓዴ ዐሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ቃል 4ኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር በአገር አቀፍ ደረጃ የአስተዳደራችን ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በተገኙበት በመዲናችን አዲስ አበባ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብሩን በድሬዳዋ አስተዳደር ለማስጀመር እየተከናወኑ ያሉ የዝግጅት ስራዎችን፤ በአስተዳደሩ ም/ቤት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የተለያዩ የችግኝ ዓይነቶችን ለመትከል እየተደረገ ያለው ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀው፤ የአስተዳደራችንን የአየር ንብረት ባገናዘበ መልኩ የችግኝ ተከላ መረሀ ግብሩ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ በዘንድሮው 4ኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር፤ 1.8 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል እና 200 ሺህ ችግኝ ለጎረቤት ሀገር ለመላክ መታቀዱም ታውቋል።


