የውይይት መድረኩ በዋናነት ወጣቱ በሀገራዊ ጉዳይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ሰላምና ልማትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ነው የተነገረው ።
የውይይት መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጄ ጸጋዬ እንደገለጹት በሀገር ግንባታም ሆነ በማህበረሰብ ለውጥ ንቅናቄ ላይ ወጣቶች የማይተካ ሚና እንዳላቸው እና የለውጡ እውን መሆን ድርሻቸው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የለውጡ ቱርፋት የሆኑትን የልማት፣ የሪፎርም ስራዎችን በመመልከት እይታውን በህብረ ቤሄራዊነት ናየአቃፊነት መርህ በመቃኝ ወጣቱ ምክንያታዊ አስተሳሰብን በማጎልበት የአካባቢውንና የሀገርን ሰላም ማስጠበቅ እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ውህደቱ የቆመባቸው ምሶሶዎች አላማዎች መርሆች እና እሴቶች በዘፈቀደ የተቀመጡ ሳይሆኑ ከሀገራችን ያለፈ ታሪክ ጥንካሬ ጉድለት ትምህርት በመውሰድ ለዛሬ ለነገ የሚሆን የለውጡ ዘለቄታነት በተጨባጭ ሊያረጋግጥ የሚችል አቅም መሰረት ያደረጉ የበርካታ ወጣቶችን ተሳትፎ ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ተናግረው ሀገራዊ ለውጡ ዘላቂነት እንዲኖረው ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም በአዲሱ የሀገር ግንባታ ላይ እንዲያውሉም አሳስበዋል።
በመድረኩም የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ወርቁ የዚህ ዘመን ወጣት ምን ማድረግ አለበት ምን ይጠበቃል ፣ለሀገር ሰላም እና እደገት የወጣቶች ሚና ፣ጽንፈኝነት፣ደካማ የሆነ የስራ ባህል ፣ወጣቶች በስሜታዊነት መገፋት፣ የለውጡ ቱርፋቶች እንዲሁም ተግዳሮቶች በሚሉ ሀሳቦች ዙሪያ ስፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶችም በርካታ ሀሳብ እና አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን መንግስት ወጣቱን የለውጥ አካል አድርጎ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ማድረጉ ለወጣቱ ትልቅ እድል ና አቅም ነው ብለዋል በተለይም በሀገር ውስጥ ናበምእራባውን ተልኮ እንዳይሰናከሉ ወጣቱ ከስሜታዊነት ወጥቶ ሀገሩን በማልማት መደገፍ እንደሚገባ ገልጸው የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ላይም ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት ሲሉም ተናግረዋል።


