በአስተዳደሩ የ9ኙ ከተማ ቀበሌ እና የ4ቱ ገጠር ክላስተር ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊዎች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ በፓርቲአችን ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውይይት የተወሰኑ ውሳኔዎች እና የስራ አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ በዛሬው እለት ውይይት አካሂደዋል።
በተካሄደው ውይይት ከሁሉ አስቀድሞ በምዕራብ ወለጋ በንፁህን ዜጎች ላይ በደረሰው ጥቃት ክፋኛ ማዘናቸውን እና ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናትን በመመኘት እንደሀገር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎች ዋና ዓላማቸው ኅብረተሰቡን ማሸበር በሆኑ ኢ-መደበኛ አጥፊ አካላት የተፈጸመው የሰው ልጆችን ህይወት የቀጠፈ ዘግናኝ ድርጊት የምንታገሰው አይደለም፣ ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደህንነትን ወደነበረበት መመለስ አሁንም ቅድሚያ የምንሰጠው ተግባራችን በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻክር አህመድ ገልጸዋል።
በተሳታፊዎች በኩልም በተለይም መንግስት ለህዝቡ የሚያደርሰውን የመረጃ ፍሰት እንዲጨምርና በቀጣይም ፓርቲው የሚመራው መንግሥት የጀመረውን የህግ ማስከበር ዘመቻ በሸኔ እና በፅንፈኛ ሃይል ላይ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል የሚደገፍ ጉዳይ መሆኑንና እንዲሁም በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥ እና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት እና ንብረት ውድመት የሚወገዝና ተቀባይነት እንደሌለው የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
በዚሁ መድረክ ሁሉም ለህዝብ ሀሳብ ቅድሚያ በመስጠት ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ አካባቢን በንቃት በመጠበቅ እና ሀገራዊ የሰላም ደህንነት ፈተናዎቻችንን እንዲገነዘበዉ በማስቻል ህዝባዊ መድረኮች እንዲካሄዱ፣ የወጣቶች የኛ ዘመን ሚና በሚል መሪ ሀሳብ ለሚደረጉ መድረኮች አቅጣጫ በመቀበል የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል ሲል የፓርቲዉ ህዝብግንኙነት ክፍል ዘግቧል


