” ምርጥ ዘር ” ህያው አላማ የሚለውን ለመወከል እንዲሁም ፀሀፊው ያሳለፋቸውን ህይወት በመቀመርና የህይወትን ፍልስፍና በመመርመር ውስጥ የተፃፈ መፅሀፍ ሲሆን ይህም በመምህር ሐይለሚካኤል ድረስ የተፃፈው ” ምርጥ ዘር ” የተሰኘው መፅሀፍም በዛሬው እለት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል ።
በዚሁም የመፅሀፍ ምረቃ ስነ-ስርአት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ኡባህ አደም በተለይም አንድን መፅሀፍ ፅፎ ለማሳተም ቡዙ ውጣ-ውረዶች እንዳሉና መምህር ሐይለሚካኤል ድረስም እነዚህን ውጣ ውረዶች በማለፍ ለዛሬው የመፅሀፍ ምረቃ ቀን በመብቃቱ መደሰታቸውን ተናግረው በድሬዳዋ ላይ የሚገኙ ሌሎች አካላትም ተሰጦአቸውን በማውጣት የከተማችን ድሬዳዋን የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ከፍ ለማድረግ መስራት እንደሚገባቸውም ነው ዶክተር ኡባህ አደም የተናገሩት ።
መምህር ሐይለሚካኤል ድረስ በዛሬው እለት ለመፅሀፍ የምረቃ ቀኑ በመድረሱ መደሰታቸውን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ሰለሞን ዘሪሁን ገልፀው ምርጥ ዘር የተሰኘው የመምህር ሐይለሚካኤል ድረስ መፅሀፍም ቡዙ ሀሳቦችን አካቶ የያዘ ጥሩ መፅሀፍ እንደሆነና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም ለመፅሀፍ መታተም ድጋፍ ማድረጉንም ዶክተር ሰለሞን ተናግረዋል ።
በድሬዳዋ አስተዳደር የኪነ-ጥበብ ምሽቶች እንዲሁም አነቃቂ የሆኑ ፕሮግራሞች ቢኖሩ ድሬዳዋን የኪነ-ጥበብም ሆነ የንግድ አውታር ማድረግ እንደሚቻል መምህር ሐይለሚካኤል ድረስ ተናግሮ ” ምርጥ ዘር ” መፅሀፍ ተፅፎ ለመታተም እንዲሁም ለምርቃት ስነ-ስርአቱ መብቃት ትልቁን አስተዋፆ ያበረከተለትን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን መምህር ሐይለሚካኤል ድረስ አመስግኗል ።
በመፅሀፍ ምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና መምህራኖች ፣ ዶክተር ወዳጄነህ መሐረ ፣ ገጣሚያን ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የመምህር ሐይለሚካኤል ድረስ ቤተሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል ።


