በተለያዩ የአለማችን ሀገራት እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ ባሉ ከተሞች ላይ የሚገኙ የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች የፍቅር የአንድነትና የመቻቻል ከተማ በሆነችው የድሬዳዋ ከተማ ላይ በሚካሄደው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ይመጣሉ ። ይኸውም ፕሮግራም ከፊታችን ሀምሌ 11 እስከ ሀምሌ 16 2014 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች በታላቅ ድምቀትም ይከበራል ።
ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት በስኬት ይከናወን ዘንድ በአስተዳደር ደረጃ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ የሚገኙ ሲሆን ለዚሁ ፕሮግራም ሲባልም በአስተዳደር ደረጃ የተዋቀረው ኮሚቴ በየሳምንቱ ማክሰኞ እና አርብ መደበኛ የኮሚቴ ስብሰባ የሚያደርግ ሲሆን ኮሚቴው በዚህ ሳምንት ባደረገው ስብሰባም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን የገመገመ ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫም በማስቀመጥ ስብሰባው ተጠናቋል ።
የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የሚመሩት ይሄው ኮሚቴም በቀጣይ ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት በከተማችን ድሬዳዋ ላይ በደመቀና ፍፁም ባማረ ሁኔታ ይከበር ዘንድም የተለያዩ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍም ይጠበቃል ።


