የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ/ 3rd Quarter.Rep. 2014abd

    መግቢያ

    የድሬዳዋ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሥሩ ያሉትን አላማ አስፈፃሚ መ/ቤቶችን የገቢዎች ባለስልጣን፣ የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት፣ የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ፤ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ጽ/ቤት እንዲሁም ለቢሮው ተጠሪ የሆኑት 2 ዋና የስራ ሂደቶችና 4 ድጋፍ ሰጪ ዳይሬክቴሬቶችን በማስተባበር ቢሮው ለመተግበር ያስቀመጣቸውን 17 ስትራቴጂክ ግቦችን በማድረግ በክልሉ የሚካሄዱ አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴዎች ለበጀት ዓመቱ በተፈቀደው በጀት መሰረት መከናወኑን ለዕቅዱ ማስፈፀሚያ ወጪ መሸፈን የሚያስችለውን ገቢ በተገቢው መሠረት መሠብሰቡን መከታተልና በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የታቀዱ የልማት ሥራዎች በተፈቀደላቸው በጀትና በታቀደላቸው ጊዜ መከናወናቸውን፤ የሪፎርም ስራዎች በቢሮው ስር ባሉ ዳይሬክቶሬቶች በእቅዳቸው መሰረት ለማከናወን በመንቀሳቀስ ላይ  ይገኛል፡፡

    በዚሁ መሠረትም በ2014 በጀት ዓመት የሪፎርም ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ በማድረግና የአገልግሎት አሰጣጣችንን ባለፉት ዘጠኝ ወራት  ከአስተዳደሩ ለመሰብሰብ ከአቀደው 1,866,423,785.44 ብር እስከ  3ኛ ሩብ ዓመት መጨረሻ ድረስ 1,488,718,064.17 የተሰበሰበ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በሥራ ላይ እንዲውል ከተፈቀደው 4,388,894,120.54 ብር ውስጥ 3,036,429,749.51  ያህል ብር ለታቀዱ የመደበኛና የተለያዩ የልማት ሥራዎች ለባለ በጀት መስሪያ ቤቶች ዝውውር በማድረግ ሥራዎቹ የተሰሩ ሲሆን ዝርዝር የዕቅድ አፈፃፀሙ እንደሚከተለው ተጠቃሎ ቀርቧል፡፡

    የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮBofed 3rd Quarter.Rep. 2014abd