የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባዔ ውይይቱን አጠናቆ አሁን ወደ ምርጫ ሂደቱ ገብቷል፡፡

    ጉባዔው በሶስት ደረጃ የሚካሄዱ ምርጫዎች ይኖሩታል፡፡ በዚሁ መሰረት የሊጉ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ምርጫ አስቀድሞ ይካሄዳል፡፡ ቀጥሎም የማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
    የማዕከላዊ ኮሚቴዎች ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ አዲሶቹ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ለብቻቸው በመሆን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ያካሂዱና ጉባኤው እንዲያፀድቅላቸው ያቀርባሉ፡፡
    የስነ ምግባር ኢንስፔክሽን አባላትን ደግሞ ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች አንድ አንድ ተወካዮች ይመረጣሉ፡፡
    ሊጉ በጥቅሉ አንድ ፕሬዝዳንትና ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶችን፣ 170 ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን 45 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን እና 11 የስነ ምግባርና ኢንስፔክሽን አባላትን እንደሚመርጥ ይጠበቃል