በሱዳን ወታደራዊ አስተዳደሩን በመቃወም በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እስካሁን አራት ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ወታደራዊ አስተዳደሩን በመቃወም በወጡ ሰልፈኞች ተቃውሞ ስትናጥ ውላለች። አሁንም በቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ እስካሁን አራት ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ሰልፈኞቹ በኦምዱርማን ከተማ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ከፀጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት መመታታቸውንም ነው ያስታወቀው። ወታደራዊ አስተዳደሩም “የሚሊየኖች ተቃውሞ” በሚል…


