ከተማ አቀፍ የሆነው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ7ሺ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 2014 ዓ.ም ለመፈተን መዘጋጀቱን የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ ስር ባሉ ጣቢያዎቹ የሚገኙ ሰባት ሺ ስልሳ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ የ ፈተና ዝግጅት አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ነጋሽ ገልጸዋል።
የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ስራዉ የተዘጋጀ ሲሆን በእለቱ የማሰራጨት ስራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡
የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ አቶ ሳሙኤል ነጋሽ እንዳብራሩት ከሆነ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በየት/ቤቶቹ የደረሰ ሲሆን ለዚህ ፈተና 70 የፈተና ጣቢያዎች መዘጋጀቱ ተገልጿል።


