ሰኔ 23,2014 ዓ.ም የክረምት ወራትን ምክንያት በማድረግ በድሬ ዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ሰፖርት ኮሚሽንና በኢትዮጵያ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚንስቴር አማካኝነት የተዘጋጀ የ2014 ዓ.ም የበጎ ፍቃደኝነት መርሃ-ግብር የአረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ፣ደም በመለገስና የአቅመደካሞች ቤት በማደስ ተጀመረ፡፡
መርሃ-ግብሩ ተናንት በ22/10/2014 ዓ.ም በሀረር ከተማ የተጀመረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በድሬደዋ የኢትዮጵያ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተከበሩ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬና የድሬ ዳዋ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ የሆኑት ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ የፌደራልና የ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተከናውኗል፡፡
በበጎ-ፍቃደኝነት መረሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬ ደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ ከ11 ክልሎችና ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ የድንበር ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኝነት ተግባር ላይ የተሳተፉ ወጣቶች፣ የድሬ ደዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን አመራሮች ፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች፣ በፕሮገራሙ ላይ የተሳተፉ የፈደራልና የከተማው ከፍተኛ አመራሮችንና የድሬ ደዋ ከተማ ህጻናት፣ወጣቶችና ነዋሪዎችን አመስግኗል፡፡
አቶ ሀርቢ ቡህ አክለውም በዚህ ክረምት ወራት እስከ 2 ሚሊየን ችግኞችን በከተማው ለመትከል መታቀዱንና በዛሬው እለትም በድሬ ዳዋ ወጠቶች አካዳሚ ተገኘተን ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ መሳተፍ ትልቅ ዕድል ነው ብሏል፡፡
በተጨማሪም የድሬ ደዋ ተወላጆችና ወዳጆችን ከተለያዩ ሀገር ውስጥም ሆነ ውጪ የሚያሰባስብ የናፍቆት ድሬ ሳምንት ከሀምሌ 11-16/2014 ዓ.ም እንድሁም የሀገራችን ከፍተኛ አመራሮች የሚገኙበት ታላቁ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ስለሚካሄድ በመረሃ-ግብሮቹ ላይም ኢንዲገኙልን በአስተዳደሩ ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በንግግራቸው ይህ የ2014 ዓ.ም የወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፍቃደኝነት ተግባር መረሃ-ግብር ትናንት በሀረር ከተማ የተጀመረና በዛሬው ዕለትም ደማቅና ውብ ከተማ በሆነችው ድሬ ዳዋም በመጀመሩ የድሬደዋ ወጣቶች ከራሳቸው አልፈው ሌሎች ማህበረሰብ የሚረዱበት፣ወጣት አጥፊ ሳይሆኑ አልሚ መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት መርሃ-ግብር ኢንዲሆንና በጋራ ሰርተን አግራችንን ከፍ የሚናረግበት መሆኑን ሁሉም ወጣቶች በዚህ በጎ ተግባር ላይ ኢንዲሳተፉ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በዕለቱ በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ ከተሳተፉት የድንበር ተሻጋሪ በጎ ፍቃደኞች መካከል ያነጋገርነው ወጣት በድሉ አዱኛ በዚህ ክረምት ወራት ብዙ ወጣቶች የእረፍት ጊዜቸውን በአልባሌ ቦታ ከሚያሳልፉ ከራሳቸው አልፈው ለአገራቸውና ለወገኖቻቸው አስተዋፅዖ የሚያበረክቱበት በተለይም አቅመ-ደካሞችን የሚረዱበት፣የተጎዱ መሰረተ-ልማቶችን የሚያድሱበትና አረንጓዴ አሻራን የሚያሳርፉበት ጊዜ ሊሆናቸው እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡


