የአፍሪካ ቀንድ የፋይናንስና ንግድ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ የንግድ አመቺ ኢኒሼቲቭ ፍኖተ ካርታ ለማጽደቅ በበየነ መረብ የተወያዩ ሲሆን ሚኒስትሮቹ በፍኖተ ካርታው ፕሮጀክቶች ዝግጅትና አተገባበር ሁኔታን ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ የኢትዮጵያ፣ የኬንያ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ እና የደቡብ ሱዳን የገንዘብና ንግድ ሚኒስትሮች እንደሁም የዓለም ባንክ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና ኢጋድን ጨምሮ ከፍተኛ የአጋር አካላት ተወካዮች መገኘታቸው ከኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ሙሀመድ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ባላፉት ጥቅት ዓመታት በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ የንግድ አመቺ ፍኖተ ካርታ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክቶች አቅርቦት ላይ ከፍተኛ መሻሻልና ለውጥ ታይቷል ብሏል።
በተጨማሪም ሁለት የኢትዮጵያ ፋይናንስ ተቋማት በቅርቡ ከአለም ባንክ ጋር ለከርሰ ምድር ውሃ ማሳለጥ፣ለአደጋ ተጋላጭነትና የአርብቶ አደር ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮጀክት እንደሁም ለለሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል የ325 ሚሊየን ዶላር ስምምነት መመፈራረማቸውና ለተግባራዊነቱንም አመርቂ ሥራዎች እየተሰራ መሆኑን አቶ አህመድ ሽዴ አስታውሰዋል።


