በሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የተዘጋጀ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የሙዚቃ አዋርድ በአዲስ አበባ ከተማ ኢሊሊ ሆቴል ተካሄዷል፡፡
በስነ ስርዓቱ ላይ በተደረገው የሙዚቃ ውድድር አሸነፊ ለሆኑ አርቲስቶች ሽልማት እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት ሀሎ ዳዌ፣ ለአርቲስት ኢብራሂም አደም እና ለአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል፡፡
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ወ/ሮ ፋንቱ ደምሱ፣ ሀጫሉ እድሜውን ልክ ለኦሮሞ ህዝብ ሲታገል እንደነበር ገልጸው፣ የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ሀጫሉ የተሰዋለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ይሰራል ብለዋል፡፡
የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የሙዚቃ አዋርዱን በቀጣይ በአፍሪካ ደረጃ ለማዘጋጀት እንደሚሰራ የገለጹት ወ/ሮ ፋንቱ፣ የሙዚቃ አዋርዱ በየዓመቱ ይካሄዳል ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡


