የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ በተገኙበት ተገምግሟል።

    የሪፎርም ስራዎች ሳምንታዊ የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም የቀረበ ሲሆን በሪፓርቱም የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ መዋቅራዊ አደረጃጀትን ወደ ቀበሌ ለማውረድ የተዘጋጀ ሰነድ ፣ የህግ ማእቀፎችን ከመለየትና ከማደራጀት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከመተግበር አንፃር: የስራ ቦታን ምቹ ከማድረግና ካይዘን በቢሮ ከመተግበር አኳያ፣ የፋይል ማኔጅመንትና ገቢን ከመሠብሠብ አንጻር እንዲሁም ከቴክኖሎጂ ልማት አኳያ የተሠሩ ዝርዝር ስራዎች ተካተዋል።
    እንዲሁም ለረጅም ጊዜው ሲሸጋጋሩ የቆዩ የመልካም አስተዳደር ስራዎች በተመለከተም የተከናወኑ ስራዎች በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች የቀረቡ ሲሆን ካሳ ክፍያ መሬት ዝግጅት ረገድ የተከናወኑ ስራዎች በቢሮው ማኔጅመንትና በሪፎርሙ ቴክኒካል ኮሚቴ ተገምግሟል።
    የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሃርቢ ቡህ እንደገለጹት ቢሮው እያከናወነ በሚገኘው የሪፎርም ስራ የሚመለከታቸው ባለሙያዎችና የስራ ኃላፊዎች ከስራ ሰአት ውጪ እያከናወኑ መሆናቸው መታዘባቸውን ገልጸው ይህም ለሪፎርም ስራው ያላቸውን ቁርጠኝነትን የሚያመላክት መሆኑን ጠቅሰው የሚበረታታ ነው ብለዋል።
    ቢሮው በቀጣይም ይህንኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
    ዘገባው የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት