የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የስራ ኃላፊዎች እንደገለፁት # የ2014 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ በተደራጀ መልኩ የሚጀመረው ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን የሚናገሩት #ኮሚሽነር _ፉራንኦል _ ለተሳታፊዎች የሚሰጠው ሥነ-ልቦናዊ እርካታ፣ ልምድ ከመለዋወጥ፣ ከመተሳሰብ፣ አብሮነትን ከማዳበርና ከማህበራዊ መስተጋብር አኳያ የሚፈጥረው ዕድል፣ እንዲሁም ለሚደረግለት ሰው የሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑን ነው የተናገሩት ።
*
#”የወጣቶችን ተሳትፎና ተነሳሽነት በተደራጀና በተቀናጀ አስተባብሮ የተሻለ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በዘንድሮው ክረምት ለማስጀመር ለዚህም ከወጣቶች ፌዴሬሽኖች እና ከተለያዩ የወጣት አደረጃጀቶች ጋር ከወዲው አስፈላጊ ዝግጅት ያደረጉ መሆኑን በኮሚሽኑ የወጣቶች ዘርፍ ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ መሐዲ ሰመር ገልፀዋል “፡፡
*
በዚህ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንቅስቃሴ በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚዎች ናቸው የሚሉት በኮሚሽኑ የወጣቶች ዘርፍ ዳሬክተሩ በተለይ አቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ፤ የማዕድ ማጋራት ፤ የአካባቢ ጥበቃና ፅዳት ፤ የሰባዊ ድጋፎች በዘንድሮው ክረምት ትኩረት የተሰጣቸው መሆናቸውን፤ ከዚህ ባለፈም «ድንበር _ተሻጋሪ» ተግባር መኖሩንም አስረድተዋል።
*
#የአረንጓዴ_አሻራ ችግኝ ተከላው በወጣቶች ፣ በስፖርቱ ቤተሰብ በአስተዳደሩ ወጣቶች አካዳሚ አካባቢ ሐሙስ ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ችግኞች የሚተከሉ መሆኑ ተጠቁሟል ፡፡
#የኮሚሽኑ _ ኮሚሽነር_ አቶ_ ፉራንኦል _ቡልቻ በበኩላቸው የተከሉ ችግኞችን በመንከባከብና እንዲፀድቁ በማድረግ ተከታታይ ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።
#”በጎነት_ ለኢትዮጵያ _ ከፍታ” _ *በ2014ዓም የድሬዳዋ የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ከወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ሐሙስ ሰኔ 23ቀን በይፋ እንደሚጀመር የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፉራንኦል ቡልቻ አመልክተዋል ፡፡


