በበጀት ዓመቱ ከተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችና በገጠር ከተያዙት መካከል በማህበራዊ ዘርፍ የአሰሊሶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ16 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ የትምህርት ዘመን ለክላስተሩ እና በዙርያው ለሚገኘው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጠው ይህ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

    ሌላኛው በዛሬው ዕለት የተመረቀው የአሰሊሶ አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ ከ 23 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትና ከ6 መቶ በላይ አርሶ አደሮች ከ90 ሄክታር በላይ መሬት እንዲያለሙ የሚያስችል ነው።