የድሬዳዋ ፖሊስ በራስ ሙሉ አቅም ለመጀመሪያ ግዜ ነው ከፍተኛና መካከለኛ አመራር መኮንኖችን አሰልጥኖ ያስመረቀው::
በመርህ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር “ፖሊስነት እውቀት፣እና አቅም ብቻ ሳይሆን ሀገር መውደድን እና ለሀገር መስዋዕትነትን መክፈል የሚያጠቃልል ሙያ መሆኑን ገልፀው ለዚህም አለማ ሁሌም መትጋት ከራስ ጥቅም ይልቅ የህዝብንና የሀገርን ጥቅም ማስቀደም የፖሊስ የሁልጊዜ ስራው ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ክቡር ከንቲባ አክለውም በቀጣይም ወደ ስራ ስትሰማሩ ህዝቡን የለ ምንም አድሎ በእኩልነትና በታማኝነት የምታገለግሉና ችገሮችን በጥበብና በፍቅር የምትፈቱና የምትሻገሩ ሊሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል ።
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው የድሬዳዋ ፖሊስ አካዳሚ በመደበኛ የፖሊስ ስልጠና ምልምል ፖሊሶችን ተቀብሎ ከ1ኛ እስከ 12ተኛው ዙር አሰልጥኖ በፖሊስነት ሞያ ሲያስመራቅ እንደነበር ገለፀው በዛሬው ዕለት ግን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ይሲጥ የነበረውን ስልጠና ዩንቨርስቲው በሠጠው ውክልና መሰረት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜው ከዋና ሳጅን ወደ ረ/ኢንስፔክተር እና ከኢንስፔተር ወደ ዋና ኢንስፔክተር የሚሸጋገሩ የፖሊስ አመራሮችን በብቃት አሰልጥኖ ማስመረቁን ተናገረዋል ።
የስልጠና ሂደቱን አስመልክቶ ሪፖርቱ የቀረቡት የፖሊስ አካዳሚ ዋና ኃላፊው ኮማንደር ኢሳያስ ኩማለ ባቀረቡት ሪፖርት የድሬዳዋ ፖሊስ አካዳሚ በ2014 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ከዋና ሳጅን ወደ ረ/ኢንስፔክተር እና ከኢንስፔተር ወደ ዋና ኢንስፔክተር የሚሸጋገሩ 104 የፖሊስ አመራሮችንና እጩ መኮንኖችን ሲያሰለጥን ቆይቶ በዛሬው ዕለት ለሚርቃት መብቃቱን ተናገረዋል ።
በምረቃ መርሀ ግብሩ በትምህርታቸው ብልጫ ውጤት ያመጡ መኮንኖች ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::
በእዚሁ የእጩ መኮንኖችና ከፍተኛ አመራሮች ምርቃ መርህ ግብር ላይ የአስተዳደሩ ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈትያ አደንን ጨምሮ ም/ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህና ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣የሀገር ሽማግሌዎች አበገዳዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና የፖሊስ አመራርና አባላት ፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ሲል ድሬ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ዘግቧል


