በነገው እለት (ሐምሌ 22ቀን 2014) በድሬደዋ አስተዳደር አዲሱ ምድር ባቡር ጣቢያ “አሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ቃል ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል አመራሮች የሚሣተፉበት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ለማካሄድ አስፈላጊውን ቅድመ-ዝግጅት ያጠናቀቀ መሆኑን የድሬደዋ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ ቴክኒክ ኮሚቴ ገልፅዋል።

    በመሆኑም ተጋባዥ እንግዶች፣ መላው የድሬደዋ አመራሮችና ነዋሪዎች በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት አሻራዎን እንድያስርፉ ጥሪ ያስተላልፋል።