በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኘውን የጎሮ ችግኝ ጣቢያ ማእከልን ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ጎበኙ ።

    በ 4 ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ችግኞችን ለመትከል የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን እነሆ አሁን ላይ በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ላይም የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር እየተካሄዱ ይገኛሉ ።
    እነዚህም ችግኞች በአስተዳደሩ ላይ በሚገኙ የችግኝ ጣቢያ ማእከሎች ላይ የሚፈሉ ሲሆን በዛሬው እለትም በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ ካሉ የችግኝ ጣቢያ ማእከሎች ውስጥ የጎሮ ችግኝ ጣቢያ ማእከልን ከፍተኛ የአስተዳደሩና የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አመራሮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ አባገዳዎች እንዲሁም ኡጋዞች ጎብኝተውታል ።
    በ 4 ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ በድሬዳዋ አስተዳደር ለመተከል ከታቀዱት 2 ሚሊዮን ከሚሆኑ ችግኞች ውስጥ 600 ሺህ የሚሆኑ ችግኞች የፍራፍሬ ችግኞች መሆናቸውም ታውቋል ።