በዛሬው እለት ” አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን ” በሚል መሪ ቃል 4 ተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት በኢትዮጲያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ጁቡቲ የባቡር መስመር ድሬዳዋ ጣቢያ ላይ ተካሂዷል ።
በዚሁም መርሀ-ግብር ላይም ከብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ፣ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፣ ከዋልታ ቲቪ ፣ ከዋፋ ማርኬቲንግና ኘሮሞሽን ጋር በጋራ በመተባበር በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ 1 ሺህ ለሚሆኑ ተማሪዎች 12 ሺህ ደብተርና 12 ሺህ እስክርቢቶዎችን ድጋፍ ተደርጓል ።
ይህንንም ድጋፍ የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ሙሉካ መሀመድና በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚማሩ ተማሪዎች ከድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና በሚኒስቴር ማእረግ የፓርቲው የሲቪክና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት የተከበሩ ዶክተር አለሙ ስሜ እጅ ተረክበዋል ።


