በዛሬዉ ዕለት በዉጪ ሀገር የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች መልካ በሚገኘዉ አቡነ አረጋዊ የሴቶች ገዳም በመገኘት የተለያዩ ድጋፎችን አበርክተዋል በድጋፍ አሰጣጥ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ለገዳሙ ለተደረገዉ ድጋፍ የተሰማቸዉን ልባዊ ደስታ የገለጹ ሲሆን ከተማችንን በማሳደግ ህብረተሰባችንን መለወጥ እንድንችል የመተባበር፣መደጋገፍ እና የመተጋገዝ ባህላችን በእጅጉ ማደግ አለበት ብለዋል ክቡር ከንቲባዉ ።
በእለቱ ለገዳሙ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን፣ ለጾም መፍቻ የሚሆን ሰንጋ እና ሌሎች ስጦታዎችን፤ ላበረከቱ የትንሿ_ኢትዮጵያ የድሬ ልጆች፤ እንዲሁም ዳቦ ቤቱን ለመገንባት ፍላጎቱን ላሳየዉ ሳንዶቃን ደበበን ክቡር ከንቲባዉ አመስግኗል።
ትውልድ የሚያንፁ እናቶቻችንን ቀሪ ጉድለት በምንችለው አቅም ለመሙላትም ዝግጁ ነን በማለትም ቃል ገብተዋል ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር
ፎቶ credit :- ከንቲባ ጽ/ቤት


