የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የ 2014 በጀት አመት የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በኢትዮ-ኢጣሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል ።

    በዚሁም የውይይት መድረክ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ\ሮ ፈቲህያ አደን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የካቢኔ አባላት ፣ የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አመራሮችና አባላት እንዲሁም የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል ።
    የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም በመድረኩ ላይ ያሉትን መረጃዎች ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል ።
    በአለማየሁ አበበ ።
    ፎቶ :- በይድነቃቸው አብርሃም ።