የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ የብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት የ2014ዓ.ም ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ተካሄደ።

    በማጠቃለያ ኮንፍረንሱ የመሠረታዊ ድርጅቱ የ2014 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የ2015 ዓ.ም እቅድ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በኮንፍረንሱ ተሳታፊ በሆኑ የፓርቲው አባላት እና አመራሮችም ሰፊ ወይይት ተደርጎበታል።
    የቀጣይም በ2014ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም የነበሩ መልካም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በመለየት እና በኮንፍረንሱ ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳቦችን በግብዓትነት በመውሰድ በ2015 ዓ.ም የመሠረታዊ ጅርጅቱን አፈፃፀም የተሻለ ለማድረግ ሁሉም አባላት እና አመራሮች የበኩላቸውን እንዲወጡም አቅጣጫ ተቀምጧል።
    ፎቶ :- ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ