የድሬዳዋ አስተዳደር የፋይናስ እና ገቢዎች የመንግስት ሰራተኞች የብልፅግና ፓርቲ መሰረታዊ ድርጅት ኮንፍረንስ አካሄዱ

    የአሰተዳደሩ ፋይናንስና ገቢዎች መሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢና የቢሮዉ ኃላፊ ክቡር አቶ ሱልጣን አሊዪና እና የመሠረታዊ ጅርጅቱ ም/ሰብሳቢና የአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አብዱሰላም መሃመድ መሪነት የፓርቲዉ መሰረታዊ ድርጅት ኮንፍረንስ በከንቲባዉ መሠብሰቢያ አዳራሽ በድምቀት ተካሄዱዋል ፡፡
    በኮንፍረንሱም ላይ የ2014 ዓም የዘርፉ መሰረታዊ ድርጅት እቅድ አፈፃፀም፤ የኦዲት ኮሚሽን ሪፖርት እንዲሁም 2015 ዓም ዕቅድ ቀርቦ ዉይይት ከተደረገበት ብኃላ የጸደቀ ሲሆን በተጨማሪ የዘርፉ መሰረታዊ ድርጅት እና የህዋሳት አመራሮችን በአድስ መልክ ለማዋቀር ዕጩዎችን ለቤቱ በማቅረብ በኮንፈረንሱ ተሳታፊ አባላት ተመርጠዋል።
    በመጨረሻም ሁለቱም ከፍተኛ አመራሮች በስተላለፉት መልዕክት በመንግስታዊ ስራም ሆነ በድርጅታዊ ስራ በተለይም ገቢን መሰብሰቡ ላይ እንደ ድርጅት አመራርና አባልነት በግንባር ቀደምነት ህዝቡን በማገልገል አርአያ መሆን ከሁሉም የፓርቲዉ አባል እንደሚጠበቅ በመተማመን የተጣለባቸዉን ድሪብ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸዉን በማረጋገጥ ኮንፈረንሱ ተጠቃሉዋል።