በገጠሩ የአስተዳደሩ ክፍል ያሉ ችግሮችን በረዥምና በአጭር ጊዜ ምላሽ ለመስጠት በቅንጅት እንደሚሰራ ተገለፀ
በዋሂል ክላስተር የህዝብ ተመራጮች ከነዋሪው ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ምንም እንኳን መንግስት ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮችን በአንፃራዊነት እየተፈታ ቢሆንም አሁንም በራከታ ተግዳሮቶች እንዳሉባቸው የክላሰተሩ ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን የውስጥ ለውጥ መንገዶች ባለመስፋፋታቸው ለችግር እየተጋለጡ መሆናቸውን /ወላድ እናቶችንም ሆነ የታመሙ ሰዎችን/ ወደ ሃኪም ቤት ለመውሰድ ጭምር እየተቸገሩ መሆናቸውን አስረድተዋ የዋና መንገድም ቢሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጎዳ በመምጣቱ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
ከትመህርት አንፃር ሁለተኛ ደረጃትምህርት ቤት እንዲገነባ ተጠይቋል።ሴቶችና ወጣቶች በትምህርት እራሳቸውን እንዲያበቁና ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲደርሱ የሚያግዙ ስራዎች መከናወን እንዳለባቸው ተገልጿል።ግብርናን በተመለከተ ምርታማነታቸውን ሊያሳድግ የሚያስችል በመስኖ የታገዘ ስራ እንዲያከናውኑ የሚያግዝ ድጋፍ እንደሚፈልጉ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።
ከኑሮ ውድነት ፣ ከወጣቶች ስራ አጥነት ፣ ከመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ የትራንስፖርት ችግር ፣ ከመብራት ጋር ተያይዞ ፣የወጣት ማእከላት መስፋፋት አኳያ ችግሮች መኖራቸውን አውስተው አንዳንድ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በጥብቅ ክትትል እንዲፈቱ የክላስተሩ ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ድሬደዋን ከወከሉ ሁለት እንደራሴዎች አንዱ የሆኑት አቶ አብዱጁሃድ መሃመድ በውይይቱ በሰጡት ማብራሪያ እንደ አገር እየታየ ያለውን የኑሮ ውድነን ለመቋቋም በድሬደዋ ደረጃ በተለያዩ መንገዶች ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
የአስተዳደሩን የገቢ መጠን ለማሳደግ ከመቼውም በላይ እየተሰራ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መሆኗ ወደፊት ለመልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አብራርተዋል።
አቶ አበወዱጁሃድ አክለውም ድሬደዋ ባለፉት ጊዜያት በነበሩ ብልሹና ውስብስብ ምክንያቶች ለተለያዩ ችግሮች ስትጋለጥ መቆየቷን አስታውሰው አሁን ላይ እንደ አገር ከመጣው ለውጥ ጋር የተቃኝ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በቀጣይም የድሬደዋን እድገት እውን የሚያደርጉ ፣ የነዋሪውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመቅረፍ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጡ ስራዎችን በጥናት በመለየት በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኙ በቅንጀት እንደሚሰራ አቶ አብዱጁሃድ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩክ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ከዚህቀደም ከክላስተሩ ነዋሪዎች ጋር ተገናኝቶ ያሉ ችግሮችን ውይይት መደረጉን አስታውሰው የሚስተዋሉ ችግሮችንለመፍታትለመፍታት ፌደራል ደረጃ እንዲሁም እንደ ድሬደዋ አስተዳደር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ምክትል አፈ ጉባኤዋ አክለውም በመድረኩ የተነሱት ጥያቄዎች በክላስተሩ በተግባር የሚስተዋሉ መሆናቸውን ገልፀው በህዝቡ በራሱ የሚፈቱ፣ በድሬደዋ አስተዳደር ደረጃ የሚፈቱ እንዲሁም በፌደራል ደረጃ የሚፈቱ መሆናቸውን አመላክተዋል።
ጥያቄዎቹ በቀጣይ በአጨርና በረዥም ጊዜ ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን በመለየት በየደረጃው ከህዝቡ ጋር በመሆን ምላሽ ለመስጠት ይሰራል ብለዋል።በመድረኩ በክላስተሩ ያሉ 9 ቀበሌዎች የተውጣጡ ሶስት መቶ የሚሆኑ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህዝብን የሚወክሉ ተወካዮች በአመት ሁለት ጊዜ ከነዋሪው ጋር ተገናኝተው በመወያየት የውክልና መወጣት ተልእኮን እንደሚያከናውኑ ለማወቅ ተችሏል።
በዳግማዊ ፍቃዱ


