እየተከላከለች እየለማች ያለች ሀገር ” በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከር የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በአሁን ሰአት በ ቢ ካፒታል ሆቴል መሰብሰብያ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል ።

    በመድረኩ ላይም የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊና የፖለቲካና ርእዮተ አለም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻኪር አህመድ ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ደረጄ ፀጋዬ
    የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የጥናት ምርምርና የሱፐርቪዥን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ገዛኸኝ ታዲዮስ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ፣ የትግራይ ተወላጆች ተሳታፊ ሆነዋል ።

    የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም በውይይት መድረኩ ላይ ያሉትን አጠቃላይ መረጃዎች ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል ።