በወባ በችኩንጉኒያ ደንጊንና ኮቪድን 19 ላይ ውይይት ተደረገ የወባ በሽታ በሞቃታማ አካባቢዎች በስፋት በሚራቡ ትንኞች የሚከሰት ከዓለማችን ፈታኝ በሽታዎች በቀዳሚነት የሚሰለፍ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በርካቶችን በየዓመቱ ለስቃይ የሚዳርገው ይህ በሽታ እንደየወቅቱና አካባቢው እየተፈራረቀ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኖ እንደ ቆየ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ዛሬ በቢ ካፒታል ሆቴል በምክክር መድረኩ ላይ በዋናነት ከተነሱ አጀንዳዎች ውስጥ ወባ፣ ችኩንጉኒያና፣ ደንጊን ከመቆጣጠር አንፃር እንደ ጤና ቢሮ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የጤና ቢሮ ሀላፊዋ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ከጋዜጠኞች ለተነሳላችው ጥያቄ ማብራሪያ ሰተዋል፡፡ ወ/ሮ ለምለም በሰጡት አስተያየት ጤና ቢሮ ከህብረተሰቡ ጋር ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንዳለና ከታችኛው አደረጃጀት ድረስ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመስከረም፣ በጥቅምት፣…


