ዛሬ በቢ ካፒታል ሆቴል በምክክር መድረኩ ላይ በዋናነት ከተነሱ አጀንዳዎች ውስጥ ወባ፣ ችኩንጉኒያና፣ ደንጊን ከመቆጣጠር አንፃር እንደ ጤና ቢሮ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የጤና ቢሮ ሀላፊዋ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ከጋዜጠኞች ለተነሳላችው ጥያቄ ማብራሪያ ሰተዋል፡፡
ወ/ሮ ለምለም በሰጡት አስተያየት ጤና ቢሮ ከህብረተሰቡ ጋር ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንዳለና ከታችኛው አደረጃጀት ድረስ ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡
በመስከረም፣ በጥቅምት፣ በህዳር ወር ወባ፣ ችኩንጉኒያና፣ ደንጊን፣ ኮቪድን ጨምሮ ሌሎች ጉንፋን መሰል በሽታዎች የሚከሰትበት ወቅት ስለሆነ ምን አይነት ቅድመ ዝግጅቶች እንደተሰሩና ምን ያህል እንዳሉ፣ ታማሚዎች ላይስ ምን ተሰራ፣ ህክምናው ምን ይመስላል፣ የጤና ባለሙያው አቅም ምን ድረስ ነው፣ እንዲሁም ምን ያህል ታማሚዎች አሉ የሚለውን አውቆ በቀጣይ ከሴክተሮች ጋር ተጋግዞ ለመስራት እንደሆነ ወ/ሮ ለምለም አብራርተዋል፡፡
ወ/ሮ ለምለም እንዳሉት ዛሬ በውይይቱ ላይ ወባ፣ ችኩንጉኒያና፣ ደንጊን፣ የድሬዳዋ መሰረታዊ ችግሮች ስለሆኑ ከተቋማቶች ጋር ተናበንና ተቀናጅተን ዜሮ ለማድረስ በምንችልበት ላይ ነው የተወያየነው ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ለምለም ለማህበረሰቡ ባስተላለፉት መልዕክት ማንኛውም ውሃ የያዘ ነገር ማስወገድና ማፋሰስ እንደሚያስፈልግ የተናገሩ ሲሆን፤ አካባቢን በቼም ቢሆን ፅዱ እና ውብ ማድረግ ለራስም እንደሚጠቅም ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም አጎበርን በአግባቡ በመጠቀም የወባ ትንኝን መከላከል እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡
አጎበር ያለ አግባብ ጥቅም ላያ እየዋለ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን እንደ ድሬዳዋ አጎበርን በሶስት ዓመት አንዴ እንደሚያገኙ የተናገሩት ወ/ሮ ለምለም በአግባቡ አጎበርን ህብረተሰባችን መጠቀም አለበት ብለዋል፡፡
ለትንኟ መራቢያ አመቺ የሆኑ ቦታዎችን ማስወገድ እንደሚያስፈልግና ፋብሪካዎች፣ ትልልቅ ሴክተር በስራቤቶች ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ይገባቸዋልም ተብሏል፡፡
ይህን መሰል መድረክ በተለያዩ ደረጃዎች የተሰጠ ሲሆን ከሀይማኖት አባቶች፣ ከቀቀበሌ አመራሮች፣ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት አድርገን የዘመቻ ስራዎችን በሰፊው ተካሂዶ የመጣ ለውጥ መኖሩን ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም የኮቪድ 19 ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ክትባቱ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡
በወባ በችኩንጉኒያ ደንጊንና ኮቪድን 19 ላይ ውይይት ተደረገ የወባ በሽታ በሞቃታማ አካባቢዎች በስፋት በሚራቡ ትንኞች የሚከሰት ከዓለማችን ፈታኝ በሽታዎች በቀዳሚነት የሚሰለፍ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በርካቶችን በየዓመቱ ለስቃይ የሚዳርገው ይህ በሽታ እንደየወቅቱና አካባቢው እየተፈራረቀ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኖ እንደ ቆየ መረጃዎች ያመለክታሉ።


