ፍሌም ኦፍ ፋየር ሚንስተሪ (Flame of Fire Ministry) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡

    ድጋፉ በድሬደዋ ከተማ በተለያዩ ቀበሌዎች እናአካባቢዎች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከድሬደዋ ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመሆን ከ1ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለጹት የሚሽን ጂሰስ ኢትዮጵያ ሚንስትሪ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል አበራ ድጋፉ የተደረገው ፍሌም ኦፍ ፋየር ሚንስተሪ ከአሜሪካ ከመጡ እህትና ወንድሞች በተሰበሰበ የገንዘብ ድጋፍ መሆን ገልጸዋል፡፡
    በዛሬው እለትም በቀበሌ 05 አስተዳደር አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት ለ110 ተማሪዎች ዩኒፎርም እና የትምህርት መርጃ መሳሪያ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
    ከድሬደዋ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመተባበር ለሳቢያን አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና መሳሪያ ድጋፋ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል ፡፡

    በተጨማሪም ልዩ ስሙ ገንደ ምስኪን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የህክምና ቁሳቁስ ፣አልባሳት፣የምግብ እና የቤት መገልገያ እቃዎችን ድጋፍ ማድረጋቸውን ሀላፊው አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡

    በቀጣይም ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት ያሉትን ችግሮች ተይተው ድጋፍ በሚሹ ጉዳዮች በትምህርት ቤቶች በሆስፒታሎችም ለይ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው ሀላፊው ያነሱት፡፡
    በድጋፉ ስነስርዓት ላይም የድሬደዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ጨምሮ የግብረሰናይ ድረጅቶች የስራ ሀላፊዎች ፣መምህራን ፣ተማሪዎች፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡