የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምላሽ እና ማብራሪያ እንዲሰጥባቸው ያሏቸውን ጥያቄዎች እያቀረቡ ነው፡፡

    እስካሁን ባለው ሂደትም እየቀረቡ ያሉ ጥያቄዎች፡-
    • የሰላም ስምምነቱ ሂደት አንድምት እና ፋይዳ ቢብራራ፤ ከማን ምን ይጠበቃል፤ በህወሓት በኩል ያለው ዝግጁነትስ እንዴት ይገለጻል?
    • የመልሶ ግንባታ ሥራዎች በጥራት፣ በፍትሐዊነት እና በፍጥነት እንዲከናወኑ የመንግሥት ዝግጁነት ምን ይመስላል?
    • የሰላም ስምምነቱ ሂደት ያልተዋጠላቸው አካላት ውሳኔዎችን ለመተግበር እንቅፋት አይሆኑም ወይ፤ ከዚህ አኳያ የመንግሥት አቋም ምንድን ነው?
    • የዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመሥራት መብት ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ፤ ዜጎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ እየተከለከሉ ነው፤ በተለያዩ አካባቢዎችም ጉልበተኞች ኬላ እየሰሩ ለኮቴ ክፈሉ እያሉ ዜጎችን እያጉላሉ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር መንግሥት ምን እየሠራ ነው?
    • የተወሰኑ የኦሮሚያ አካባቢዎችን ከአሸባሪው ሸኔ ነጻ ለማውጣት ምን እየተሠራ ነው፤ አሁንም የሽብር ቡድኑ ጉዳት እያደረሰ ነው፤ ዜጎችን እያንገላታ ነው፤ ስለሆነም ችግሩን እንዴት ለመፍታት ነው የታሰበው?
    • የምርት አቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም አለ፤ ሕዝቡ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ነው፤ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ንረት አለ፤ ችግሩን በአጭር ጊዜ እና በዘላቂነት ለመፍታ ምን እየተሠራ ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።
    ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመላቀቅ ዋጋ እየተከፈለ ቢሆንም፤ አሁንም የመልካም አስተዳደር ችግር የለውጥ ኃይሉን እየፈተነው ነው፤ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት የያዘው ዝርዝር ዕቅድ ምንድን ነው?
    • ዲጂታል ዲፕሎማሲ እንደ ውጭ ግኝኙነት ሥራ በትኩረት እንዲከናወን ከማድረግ አንጻ ምን እየተሠራ ያለው ስራ?
    • በነጻ ለሚገኙ አገልግሎቶች ክፍያ እንደመደበኛ አሠራር እየተስፋፋ እና እየተጠየቀ ነው፤ መንግሥት እዚህ ላይ ምን እርምጃ ለመውሰድ አስቧል?
    • የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ መንግሥት ያሰበው ማሻሻያ ካለ ቢብራራ