በዛሬው እለት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህውሀት ቡድን በተደረሱት የሰላም ስምምነት ዙሪያ ከሀይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች ፣ኡጋዞች ፣አባገዳዎች እና ከማህበረሰብ አንቂዎች ጋር በከንቲባ ጽ/ቤት አዳራሽ ውይይት ተደረገ፡፡
ውይይቱ በዋናነት በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት በተካሄደው የሰላም ስምምነት ዙሪያ በተደረሱት ዋና ዋና የሰላም አጀንዳዎች በሚመለከት ሲሆን ፤በተደረሱትም ስምምነቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሮ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ለስምምነቱ መጸናት የበኩሉን አስተዋእጾ እንዲያደርግ ታሳቢ ያደረገ መድረክ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ከወትሮውም ጀምሮ ኢትዮጵያ ተገዳ በገባችበት ጦርነት ውስጥ በተገኝው የሰላም አማራጭ ሁሉ መንግስት እጅን በመዘርጋት በርካታ ሙከራዎች ቢደረግም ሳይሳካ ሀገሪቱ ለሁለት አመታት በጦርነት ውስጥ ቆይታለች፡፡ በዚህም ጦርነት ውስጥ ውድ የሆነው የሰው ልጅ ህይወት ከመጥፋት አንስቶ በርካታ ቁሳዊ ውድመት መድረሱም ይታወቃል ፡፡ በመሆኑም እንደ ሀገር የመጨረሻ አማራጭ አድርጎ የተገባበት ጠርነት ለመቋጨት እና የሀገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተማ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህውሀት መካከል የሰላም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በመድረኩም የድሬደዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር እንደተናገሩት የተደረሰው የሰላም ስምምነት ለህዝቡ እፎይታን እና ድልን የሰጠ ፤ሀገሪቱን ወደ ልማት ለመመለስ በር የከፈተ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ ከድር ጁሀር ስምምነቱ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ያስጠበቀ ስምምነት መፈጸሙን ነው የገለጹት፡፡
የግዛት አንድነትን በሚመለከትም በሀገሪቱ እንድ የፌ.ደ.ራ.ል መንግስት እንዳለ ህውሀት በስምምነት ያረጋገጠበት መሆኑን ተናግረው አክለውም በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ በማቋቋም እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በቀጣይ በስምምነቱ ተፈጻሚነት የሚታዩ መሆኑንም ነው የገለጹት ፡፡
በውይይት መድረኩም በተደረሱት የሰላም አጀንዳዎች ዙሪያ ጸሁፍ ያቀረቡት የድሬዳዋ ብልጽግና ፓርቲ ምክትል የፖለቲካና ርዕዮተ አለም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻኪር አህመድ በተደረሱት ሰባት የሰላም ስምምነት ነጥቦች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዋናነት በደቡብ አፍሪካ በተደረገው ስምምነት በኢትዮጵያ መሰረታዊ ፍላጎት መከበር ላይ አቋም ይዞ በድል መጠናቀቁን ነው ሀላፊው የገለጹት፡፡
መንግስት ለሰላም ያለው ዝግጁነት በሚመለከት ፡- ህውሀት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ እና የሀገር ሉዓላዊነትን በመዳፈር በግዳጅ የተገባ ጦርነት መሆኑን እንዲሁም በዚህም ህግ የማስከበር ዘመቻ በተለያየ ጊዜ ለሰላም ዝግጁነቱን ቢያሣይም ህውሀት የሰላም ዝግጁነቱን ወደ ጎን በመተው ለ3ኛ ጊዜ ጦርነት መክፈቱን ተናግረዋል፡፡
ህውሀት ዘግይቶም ቢሆን በተቀበለው የሰላም ስምምነት በደም የተከበረ መሰዋትነት መሆኑን መዘንጋት የለበትም ነው ያሉት ሀላፊው
በቀረበው የሰላም ስምምነት አጀንዳዎች ላይም ከተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየ ተሰጥተው ውይይት ተደርጎባቸዋ፡፡
በመጨረሻም በተነሱ ሀሳቦች ዙሪያ ምላሽ የሰጡት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንደገለጹት በደቡብ አፍሪካ የተደረሰውን ስምምነት በዋናነት የድርድሩ ስኬት የተገኝው ኢትዮጵያ በሰራቸው እልህ አስጨራሽ ወታደራዊ እርምጃ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሰላም ድርድሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተደረገበት መሆኑ፣ የህዝብን ጥቅም ያሰከበረ የሀገር ደህንነትን ባስጠበቀ መልኩ መሆኑ፣ ህገ መንግስቱን መሰረት በማድረግ የተከናወነ መሆኑ እንዲሁም ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱም በመጀመሪያዎች 10 ቀናት ከባድ መሳሪያዎችን የያዙትን የማስፈታት በተጨማሪም ክልሉን በማስተዳደር በኩልም ቡዱኑ ለፌ.ደ.ራ.ል መንግስት የሚስረከብ መሆኑን በስመምምነቱ መረጋገጡን ሀላፊው ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህውሀት ቡድን በተደረሰው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡


