በመጀመሪያ ለመላዉ የአሰተዳደራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ የሠላም የጤና እና የፍቅር እንድሆንልን እመኛለሁ
በአሰተዳደራችን ህዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና በማጠጣት እንዲሁም የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር እንዲያከብር በዚህ አጋጣሚ ለመላዉ የእምነቱ ተከታዮች መልዕክቴን ለማሰተላለፍ እወዳለሁ።
በዓሉን የሚያከብረዉ ህዝበ ክርስትያኑን ጨምሮ መላው የአሰተዳደራችን ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጎልበት እንዲሁም በከተማም ሆነ በገጠር ቀበሌዎቻችን የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የልማት ተግባራት ላይ ተሳትፎአቸዉን በማጠናከር ሁለንተናዊ ብልጽግናን እዉን በማድረግ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ በአንድነት መረባረብ እንዳለበት በዚህ አጋጣሚ ጥሪዮን እያሰተላለፍኩ በድጋሚ በዓሉም የሰላም ፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።
መልካም በዓል!
አቶ ብሩክ ፈለቀ
የድ/ዳ/አሰ/የመንግስት ኮ/ጉ/ቢሮ ኃላፊ
ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም


