#ዜናሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

#DGC የካቲት23/2016

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በጋራ ለመስራት የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል::

ሁለቱ ከተሞች በቀጣይ በሰው ተኮር ፣ በአቅም ግንባታ ፣ በልምድ ልውውጥ እንዲሁም በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ በጋራ ለመስራት የተግባቡ ሲሆን÷ ስምምነቱን የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ተፈራርመዋል::

በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልምድና ተሞክሮዎቹን ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ገልፀው ልበ ቀና ባለሃብቶችን በማስተባበር ለድሬዳዋ ከተማ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን ለመገንባት ቃል መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የድሬዳዋ ከንቲባ ከድር ጁሀር ÷አዲስ አበባ ከሀገራችን አልፎ ለዓለም ከተሞች ልምድ የምታካፍል ከተማ መሆኗን ገልፀው ይህንን የዳበረና ስኬታማ ተሞክሮ ወስደን በከተማችን ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ ተግባራዊ እናደርጋለን ብለዋል::ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *