#ዜና | ህብረተሰቡ በፍትህ ዘርፍ ለሚያነሳቸዉ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተገቢዉን ምላሽ በመስጠት ተአማኒነት ያለዉ የፍትህ ስርአትን መገንባት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

#DGC | የካቲት 2016 ዓ.ም

በሶሰተኛ ዙር ለፍ/ቤት ዳኞች፣ዐ/ህጎችና ሌሎች የህግ ባለሞያዎች ሲሰጥ የነበረ የአቅም ማጎልበቻ ስለጠና ተጠናቋል ።

በ3ኛ ዙር ለፍ/ቤት ዳኞች፣ዐ/ህጎችናሌሎች የህግ ባለሞያዎችሲሰጥ በነበረ የአቅም ማጎልበቻ ስለጠና መድረክ መጠናቀቂያ ላይ ተገኝተዉ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት እና መልእክት ያስተላለፉት የፌደራልና የድሬዳዋ የፍትህ ተቋማት የጋራ መድረክ ሰብሳቢ ተወካይና የድ/ዳ ፖሊስ ወ/ል/ም/ ዘርፍ ሃላፊ ም/ኮሚሽነር ማኦ ተሾመ” ተአማኝ፣ ፈጣንና ተደራሽ የሆነ የፍትህ ስርአትን እዉን ለማድረግ በዋነኝነት ከህብረተሰብ ለሚነሱ የፍትህ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ዉጤታማ የሆነ አሰራርን በተከተለ መልኩ ምላሽ መስጠት ይገባል ነዉ ያሉት

ለእዚህም ብቁ ገለልተኛና ተጠያቂነት ያለበት የፍትህ አሰራር ስርአትን እዉን ማድረግ ያሻል ያሉት ም/ኮሚሽነሩ አሁን ላይ ለእዚሁ ተግባራዊነት እንደ ሀገርም ሆነ አስተዳደር የፍትህ ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ነዉ ያሉት።

ም/ኮሚሽነሩ አያይዘዉም በፍትህ ሪፎርም ዉስጥ የማስፈፀም አቅምን ማሳደግ ዋንኛ ጉዳይ እንደመሆኑ በተመረጡ የህግ ርእስ ጉዳዮች ላይ ስልጠናዎች አየተሰጡ ያሉና በቀጣይም የሚሰጡ ይሆናል ያሉ ሲሆን የስልጠና ተሳታፊዎችም ከሰልጠና መድረኮች የሚገኙትን ተጨማሪ እዉቀትና ግንዛቤዎችን ወደ ተግባር በመቀየር በፍትህ ዘርፍ ለዉጦችን ለማምጣት ይበልጥ መታጋት ይኖርባችሃል ሲሉ ነዉ የተናገሩት ።

የተጎራባች ክልሎች የፍትህ አካላትን ትብብርና ጥምረት ይበልጥ በሚያሳደግ መልኩ ያለፉ ሁለት ዙሮችን ጨምሮ በ3ኛ ዙር የተሰጠዉ ስልጠናዉ ስኬታማ እንደ ነበር ደሞ የተናገሩት የኦሮሚያ የህግና ጥናትና ምርምር ዋና ዳሪክተር አቶ ዶባ ዳባ የሚሰጡ ስልጠናዎች በራሳቸዉ ግብ ባለመሆናቸዉ ሰልጣኞች በቀጣይ በስራ ላይ በማዋል በተግባር መረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ነዉ አፅኖት ሰጥተዉ የተናገሩት፣ የተጀመሩ የትብብርና ድጋፍ ስራዎች ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ በማረጋገጥ።

የድሬዳዋ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ከኦሮሚያ የህግና ጥናትና ምርምር ኢንስቲቲዮት ጋር በመተባበር በፍትህ ዘርፍ የዳኞች አ/ህጎችና ሌሎች የህግ ባለሞያዎችን አቅም ለማሳደግ እየሰጠ ባለዉ ስልጠና የአለፉ ሁለት ዙሮችን ጨምሮ በ3ኛ ዙር ከድሬዳዋ ከኦሮሚያ ምስራቅና ምእራብ ሀረርጌ እንዲሁም ከሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን የተዉጣጡ የፍ/ቤት ዳኞች፣ዐ/ህጎችናሌሎች የህግ ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ይሄዉ በፍትህ ዘርፉ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ይበልጥ የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ እየተሰጠ ያለዉ ስልጠና በቀጣይም በተለያዩ በተመረጡ የህግ አዋጅና ድንጋጌዎች ዙሪያ በ5 ዙሮች የሚቀጥልም ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *