ሴቶችን በስራ ቦታቸው ላይ ብቁ ውጤታማ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የመደገፍ እና ወደ አመራርነት የማምጣት ስራን ትኩረት ሰቶ እየሰራ እንደሚገኝ የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ባለስልጣን አስታወቀ

በባለስልጣኑ አለም አቀፉ የሴቶች ቀን ማርች 8 “ሴቶችን እናብቃ ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀግብሮች ተከብሯል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ በኢትዮጵያ ለ48ኛ ግዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአስተዳደራችን በተለያዩ መርሀግብሮች እየተከበረ ሲገኝ በድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ባለስልጣን የሚገኙ ሰራተኞችም እለቱን በተለያዩ መርሀግብሮች አክብረውታል።

በዚሁ መርሀግብር መክፈቻ ላይ የተቋሙን ሀላፊ በመወከል የተቋሙ የእቅድ ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አለኝታ አባይነህ እንደተናገሩት እንደተቋም ከግማሽ ፐርሰንት በላይ የሆኑ የተቋሙን ሴት ሰራተኞች አቅማቸው ጎልብቶ በተቋማዊ ስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል የተለያዩ ስልጠናዎችን በማመቻቸት እና በመረጡት እና አቅም ችሎታ እና የትምህርት ዝግጅቱ ባላቸው ቦታ ላይ ተመድበው እንዲሰሩ እድል በመፈጠር ላይ ይገኛል ብለዋል።

በዚሁ መሰረት በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፍ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም መብትና ደህንነታቸውን ለማስከበር፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ አድሎዎች እንዳይኖሩ በመታገል ረገድም እንደባለስልጣን መስሪያቤት ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በእለቱም ቀኑን የተመለከተ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

መረጃው የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ

ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *