በዚህ የሰልጣኞች የምርቃት ፕሮግራም ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር ሀርቢ ቡህ በመገኘት ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አቶ ሀርቢ ተመራቂዎችን በቀጣይ በተለያዩ ፋብሪካዎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በምትቀላቀሉበት ወቅት በስነ-ምግባር የታነፃችሁና በታታሪነት የምታገለግሉ መሆን ይገባቹሀል በማለት የመከሩ ሲሆን፤ ለዚህ መርሀ ግብር መሳካትም አስታዎፆ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በበኩላቸው ለተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በስልጠናው ወቅት ያሳዩትን የስራ ተነሳሽነትና ስነ-ምግባር በቀጣይም እንዲያጠናክሩት ተናግረዋል።
በተለይም አሁን ላይ በድሬዳዋ ኢንደስትሪ እየተስፋፋ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወጣቱም አስፈላጊውን ስነ-ግባርና ክህሎት አግኝቶ ዘርፉን እንዲቀላቀል እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎች ከፍተኛ ሚና አንዳላቸው የገለፁት ደግሞ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ዳንኤል ተሬሳ ናቸው።
አቶ ዳንኤል አያይዘውም ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የወጣት ስራ አጦችን ቁጥር በመቀነሱ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
ተመራቂዎች በበኩላቸው በስልጠና ቆይታቸው በርካታ ክህሎት እንዳገኙ ገልፀው ለስልጠናው አዘጋጆችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


