ከተለያዩ ክልል ግብርና ቢሮ የተወጣጡ ባለሞያዎችና የዘርፉ አመራሮች በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ላይ አመታዊ ግምገማና ስልጠና ተጀምሯል።
የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ፣የአለም ባንክ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራምና የክልል ስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ባለሙያዎች በአስተዳደሩ በግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ኘሮግራም የተሰሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በሁሉል ሞጆ፣ ዱጁማ፣ ኢጀአነኒ ፣ጀሎበሊና ገንደሪጌ ገጠር ወረዳዎች የተሰሩ አነስተኛ መስኖ ልማት ስራዎችን፣ የጎርፍ አደጋና የመሬት መሸራተትን ለመቀነስ የተሰሩ ግድቦችን፤ በዶሮ እርባታ ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችና ህብረት ሥራ ማህበር የስራ እንቅስቃሴዎችን ተዟዙረው የፕሮግራሙን አፈፃፀም ጎብኝተዋል።
የግብርና ሚኒስቴር የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ፣የአለም ባንክ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም እና የክልል ስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች በድሬዳዋ አስተዳደር በግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ኘሮግራም የተሰሩ የልማት ስራዎችን የገመገሙበት 5 ቀናት የሚቆይ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ፕሮግራሙ በአስተዳደሩ ለሚኖሩ ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል ከመፍጠሩ ባሻገር ከተረጂነት በማላቀቅ የአርሶ እና የአርብቶ አደር ሂወት በተጨባጭ ማሻሻል መቻሉን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም እንደ አስተዳደር የአርሶአደሩን ህይወት ከማሻሻል ባሻገር ዘላቂ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራን ማረጋገጥ መቻሉንም ጨምረው ገልጸዋል።
የግብርና ሚኒስቴር የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ፣የአለም ባንክ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአስተዳደሩ ገጠር ወረዳ የተሰሩት የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎች እና በውስን መሬት ላይ የለሙት የግብርና ወጤቶች የሰው ልጅ ጠንክሮ ከሰራ ያለመውንና ያሰበውን ማሳካት እንደሚችል ማሳያዎች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
የግብርና ሚኒስቴር የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በተለያዩ ክልል በዓለም ባንክ በሚደግፍ ፕሮጀክት የዜጎችን ዘላቂ የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል።
ምንጭ፦dire tv


