#DGC መስከረም 22/2017
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ 2016 ዓ.ም በስራ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ፖሊስ ጣቢያዎች እውቅና መስጠት እንዲሁም ተቋሙን ለረጅም አመታት ያገለገሉ አመራር እና አባላት በጡረታ በክብር የመሸኘት መርሀ-ግብርም ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች እንዲሁም የፖሊስ ኮሚሽን አመራር እና አባላት በተገኙበት አካሂዷል ።
በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ድሬዳዋ ፖሊስ በተለይም ከለውጡ በኋላ የሚታዩ በርካታ የለውጥ ስራዎች መሰራት መቻሉን ገልፀው ለነዚህም ስራዎች መሳካት የፖሊስ ኮሚሽኑ አመራር እና አባላት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፆም ክቡር ከንቲባው በእለቱም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አመራር እና አባላት በተለይም ፖሊስ ኮሚሽኑ አሁን ላይ ለደረሰበት ሁለንተናዊ ለውጥ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከታቸውን በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ተናግረው ተቋሙ አሁን ላይ እየሰራ ያለውን ውጤታማ ስራዎች በቀጣይም አጠናክሮ ሊያስቀጥል እንደሚገባም ነው አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ያስታወቁት ።
የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ያካሄደው መርሀ- ግብር በተለይም በ 2016 ዓ.ም በላቀ የስራ አፈፃፀም ለሰሩ ፖሊስ ጣቢያዎች እውቅና መስጠት ፣ በዘመናቸው ፖሊስን ያገለገሉ የሰራዊቱ አመራርና አባላት በክብር መሸኘት ፣ በላቀ ስራቸው በፖሊስ ውስጥ ምሳሌ የሆኑ አመራር እና አባላት እውቅና መስጠት ፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ከለውጡ አንዱ የሆነውን ቴክኖሎጂ 6 ተኛውን ሶፍትዌር ማስተዋወቅ እንዲሁም ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ለመስጠት መርሀ-ግብሩ መዘጋጀቱን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ ተናግረው ለነዚህ ስራዎች ሁሉ መሳካት ከፍተኛ አስተዋፆ ላበረከቱም በእለቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የድሬዳዋ ፖሊስ በከተማ ሆነ በገጠር ሰላም እና ፀጥታን በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ከሰራቸው ዘርፈ-ብዙ ስራዎች ባሻገር በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ በመሰሳተፍ በርካታ ስራዎች መስራታቸውን ምክትል ኮሚሽነር ውቢት በፍቃዱ ገልፀው ፖሊስ ኮሚሽኑ በ 2016 ዓ.ም የሰራቸውን ስራዎች በያዝነው አመትም አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራም ነው የተናገሩት ።
በመርሀ-ግብሩም ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ፖሊስ ጣቢያዎች ፣ ለተቋሙ አመራር እና አባላት ፣ ከተቋሙ ጋር በጋራ ሲሰሩ የነበሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና አጋር አካላት እንዲሁም በክብር ለተሸኙ የተቋሙ የፖሊስ አባላት እና አመራሮች ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ የእውቅና ሰርተፍኬት ፣ የገንዘብ እና የአይነት ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- በአብይ ሽመልስ







