ያለፉት ሁለት ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን አሳይተዋል፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያለፉት ሁለት ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን አሳይተዋል ሲሉ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፤ የማክሮኢኮኖሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ተሰብስቦ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም አካል የሆነውን እና በቅርብ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አፈፃፀም ገምግመናል ሲሉ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ገልጸዋል።

ፖሊሲው ተፈፃሚ በሆነባቸው ሁለት ወራት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ከባቢን መመልከት ችለናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በተመሳሳይም የገቢ ግባችንም የተቀመጠለትን ግብ በመምታት በታለመለት መንገድ ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

በአጠቃላይም ያለፉት ሁለት ወራት ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን አሳይተዋል ሲሉ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *