በኢትዮጵያና ሩሲያ ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሰረተው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መቀጠሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ውይይት አድርገዋል።
ይህን በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ በሁለትዮሽ መድረካችን ወቅት ላደረግነው ጥልቅ ውይይት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን አመሰግናለሁ ብለዋል።
በሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ቁርኝት ላይ የተመሠረተው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ መቀጠሉንም ጠቅሰዋል።
“ከዚህ በተጨማሪ የጋራችን የሆነው የብሪክስ መድረክ ሰፋ ላለ የኢኮኖሚ ትብብር እንድንሰራ በር ከፍቶልናል” ሲሉም አክለዋል።


