በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር እና የኑሮ ውድነትን ከመቀነስ ረገድ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች አቅርቦት መከናወኑ ተገለፀ

የ 2017 በጀት አመት የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚ ተቋማት የመጀመሪያው ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እየቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ በአስተዳደሩ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር እና የኑሮ ውድነት በመቀነስ ረገድ በ 2017 በጀት አመት መጀመሪያ የነበረውን 28 በመቶ የዋጋ ንረት እና የ 23 በመቶ የምግብ እና ምግብ ነክ ሸቀጦች የዋጋ ንረት ከ 10 በመቶ በታች ለማድረግ በተያዘው እቅድ በበጀት አመቱ በተለይ ከምግብ ጋር የተያያዙ የኑሮ ውድነት ሁኔታዎችን ለማረጋጋት መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች አቅርቦት መከናወኑም ተገልፆል ።

የአስተዳደሩን ገቢ በተመለከተ በአስተዳደር ደረጃ 6.3 ቢሊዮን ብር በበጀት አመቱ ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ከዚህ ውስጥም ባለፍት 3 ወራት 1.57 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1.27 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ይህም 80.7 ፐርሰንት አፈፃፀም መሆኑም ተገልፆል ። ከዚህ ውስጥም መንግስታዊ ታክስ 1,249,273,249 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1,063,918,492 ብር (85.2) ለመሰብሰብ መቻሉም ተገልፆል ። የማዘጋጃ ቤታዊን ገቢ በተመለከተ በሩብ አመቱ የታቀደው 326,140,832 ሲሆን 208,947,346 ሲሆን ( 64 ) ፐርሰንት መሆኑም በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል ።

የህብረት ስራ ግብአትና ግብይት ልማትን በተመለከተ ዘመናዊ የግብአትና ግብይት ስርአትን ከማጠናከር አኳያ በሩብ አመቱ 15 የህብረት ስራ ማህበራት ለማደራጀት ታቅዶ 14 የተደራጁ ሲሆን 53 ማህበራትን ለማጠናከር ታቅዶ 53 ማህበራትን ለማጠናከር የተቻለ ሲሆን በዚህም 1112 አባላት ለማፍራት ታቅዶ 1739 (63.9) አባላት ማፍራት መቻሉም ተገልፆል ። ከኢንቨስመንት ጋር ተያይዞ ለኢንቨስትመንት ፍሰት በተደረገው ትኩረት በሩብ አመቱ 1,625 ቢሊዮን ካፒታል ያስመዘገቡ 75 ባለሀብቶችን ለመሳብ የተቻለ ሲሆን እነዚህ ኢንቨስትመንቶች ወደ ስራ ሲገቡም ለ 924 ስራ ፈላጊዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ ስራ እድል ሊፈጥሩ እንደሚችሉም ነው በሪፖርቱ ላይ የተገለፀው ።

የስነ ተዋልዶና እናቶች የጤና አገልግሎት ማሻሻል ጋር ተያይዞ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተቀባይነት ሽፋን በተመለከተ በበጀት አመቱ መነሻ ላይ ተደራሽ የነበረውን 44 በመቶ ሽፋን በሶስት ወሩ ለተጨማሪ 93,340 ዜጎች ተደራሽ በማድረግ ወደ 44 በመቶ ሽፋን ለማሳደግ የታቀደ ቢሆንም ከእቅዱ በታች 51,960 ተጨማሪ እናቶችን ብቻ ተደራሽ ማድረግ በመቻሉ የአገልግሎት ሽፋኑ ወደ 40 በመቶ ሽፋን በማሳደግ ከሩብ አመቱ እቅድ አንፃር የ 91 በመቶ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ ተገልፆል ።

ከትምህርት ልማት ጋር ተያይዞ በትምህርት ቤት በቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ላይ በተደረገ ጥናት በሩብ አመቱ የትምህርት ቤቶች መክፈቻ ወቅት እንደመሆኑ መጠን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ላይ ጥገና ለማድረግ እንዲያስችል በ 10 ትምህርት ቤቶች በእቅድ በተያዘው መሰረት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ የብልሽት ልየታ በማድረግ ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች ፣ ሚኒላፕቶፖችና የኢንተርኔት ዝርጋታዎች ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ሁሉንም በመጠገን በእስታንዳርድ መሰረት ማደራጀት መቻሉም ነው በሪፖርቱ ላይ የተገለፀው ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- በአገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *