ተቋማዊ አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል አንፃር በሩብ አመቱ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ ።

#DGC | ጥቅምት 14 / 2017 ዓ.ም

የ 2017 በጀት አመት የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚ ተቋማት የመጀመሪያው ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀጠለ ሲሆን በሪፖርቱም የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ውጤታማነትን ከማሻሻል በ 11 ተቋማት ለ 1,141 አመራርና ፈፃሚዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ 1,199 አመራርና ፈፃሚዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት የተቻለ ሲሆን በ 13 ተቋማት ለ 289 ሰራተኞች በስራ አፈፃፀም ውጤታቸው እውቅና እና ማበረታቻ ለመስጠት ታቅዶ በሩብ አመቱ ለ 329 ፈፃሚዎች እውቅና እና ማበረታቻ መስጠት መቻሉም ተገልፆል ።

ተቋማዊ አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል አንፃር በሩብ አመቱ በ 13 ተቋማት 207 የአገልግሎት ስታንዳርዶችን ለማስመዝገብ ታቅዶ በ 11 ተቋማት 207 አገልግሎቶችን ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን በሩብ አመቱ በ 6 ተቋማት 956 ሰራተኞችን በስራ አፈፃፀም ለመመዘን ታቅዶ 992 ሰራተኞችን በስራ አፈፃፀም ለመመዘን መቻሉም ተገልፆል ።

የሴቶችና ማህበራዊ ተሳታፊነትን በተመለከተ በ 4 ተቋማት 29 ሴቶችን የህፃናት ማቆያ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 25 ሴቶችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ የተቻለ ሲሆን የግንባር ቀደም ሴቶችን ልየታ በተመለከተ በ 4 ተቋማት 39 ግንባር ቀደም ሴቶች ልየታ ለማድረግ መቻሉም ተገልፆል ።

ለአቅመ ደካማ ወገኖቻችን የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን በተመለከተ በ 16 ተቋማት 82 መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ 78 መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ተችሏል ። ከደም ልገሳ ጋር በተያያዘ በ 17 ተቋማት 216 ሰራተኞች የደም ልገሳ እንዲያደርጉ ከተያዘው እቅድ ውስጥ በሩብ አመቱ 228 ሰራተኞች የደም ልገሳ እንዲያደርጉ ማስቻሉን እና የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎችን በተመለከተ በሩብ አመቱ በ 20 ተቋማት 5,353 ተማሪዎችን ለመደገፍ ታቅዶ 5,076 ተማሪዎች የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ እና ድጋፍ እንዲያገኙ መደረጉም ተገልፆል ።

ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ የስራ አጥነት ምጣኔን በተመለከተ በአስተዳደራችን በ 2017 በጀት አመትና በ 2016 በጀት አመት መጨረሻ ከሚገመትበት የ 19 በመቶ ወደ 18 በመቶ በታች ለማድረስ ታቅዷል ። በዚህም መሰረት በዓመቱ 19,000 ስራ ፈላጊዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ በሩብ አመቱ 1,384 መመዝገብ መቻሉም ተገልፆል ።

በከተማ በአጠቃላይ ለ 2,726 ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን በዚህም ወንድ 1,565 ሴት 1,161 እንደሆነና ከዚህ ውስጥ ቋሚ የስራ እድል ለ 2,045 ተጠቃሚዎች የተፈጠረ ሲሆን ወንድ 1,144 ሴት 901 ናቸው ጊዜያዊ የስራ እድል። ደግሞ ለ 553 ስራ ፈላጊዎች ስራ ለመፍጠር ታቅዶ ለ 681 ስራ ፈላጊዎች ስራ መፍጠር መቻሉንም ነው በሪፖርቱ ላይ የተገለፀው ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- አገኘው ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *