የ 2017 በጀት አመት የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚ ተቋማት የመጀመሪያው ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱም በ 2017 በጀት አመት በአስተዳደራችን በገጠርም በከተማም በሀገር ሆነ በአስተዳደራችን ደረጃ የተቀመጠውን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እና ባለፍት አመታት የተጀመሩ ስራዎችን ለማጠናከር በርካታ ስራዎች ታቅደው ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል ።

#DGC | ጥቅምት 14 / 2017 ዓ.ም

በዚህም መሰረት የአስተዳደሩ መንግስት የማስፈፀም አቅም በማጎልበት የዜጎችን እርካታ ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር ተደማሪ ውጤት ሊያመጡ የሚያስችሉ ስራዎች ታቅደው በእቅዳቸው መሰረት የመጀመሪያ ሩብ አመት ስራዎች መከናወናቸውም ተገልፃል ። በመጀመሪያው ሩብ አመት በዋናነት የዝግጅት ምእራፍ ስራዎች እና የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች በትኩረት እንዲከናወኑ ከማድረግ ባሻገር አበይት ተግባራት መከናወናቸውም ነው በሪፖርቱ ላይ የተገለፀው ።

በ 2017 በጀት አመትም የአስተዳደራችን ዋናኛ የትኩረት መስኮችም በዋናነት በገጠር ከተረጂነት የመላቀቅ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እና ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ ፣ የዋጋ ግሽበትን የኑሮ ውድነት የሚያስከትለውን ጫና መቀነስና ማረጋጋት ፣ የስራ እድል ፈጠራ በገጠርም በከተማም እንዲኖር ማስቻል ፣ በከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በቅንጅትና በፍጥነት የማከናወንና ምቹና ዘመናዊ ከተማ ማድረግ ፣ በኢንዱስትሪ ዘርፍ በተለይም የአምራች ዘርፍን የማምረት አቅም በማሳደግ ተጨማሪ የስራ እድል እንዲፈጥር የማድረግ ፣ በማህበራዊ አገልግሎት ረገድ የትምህርት እና ጤና ተደራሽነትና ጥራትን የማረጋገጥ በመሰረተ ልማት ረገድ የአስተዳደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያሳልጡ የመንገድ ግንባታዎች የንፁህ መጠጥ ውሀ ተደራሽ ፣ በሰላም በፍትህና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት መሆናቸውም ተገልፃል ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ :- አገኘው ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *