ሀገራችን ኢትዮጵያ በወረሀ መጋቢት ሀገራዊ ለውጦችን ያስመዘገበችበት እና ግዙፍ የኢትዮያን ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ያስቀመጠችበት እንዲሁም የለውጡ መንግስት መጋቢት 24 /2010ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት እና ቃለ መሀላ የፈፀሙበት እነዚህና መሰል ሀገራዊ ለውጦች የተመዘገቡበት ወር በመሆኑ የድሬዳዋ አስተዳደር ወሩን በተለያዩ ሁነቶች ለማክበር እንቅስቃሴዋችን በማድረግ ላይ ይገኛል።
እስተዳደሩ ”የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች!”በሚል መሪ ቃል ለሚዘከረው ወረሀ መጋቢት የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራው የተቀናጀ እና ፈጣን መረጀዋችን ለህብረተሰቡ ለማድረስ ከባለድርሻ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን አብይ ኮሚቴዋች በቀጣይ በሚኖሩ የስራ እንቅስቃሴዋች ላይ ውይይት አድርጓል።


