ፕሮግራሙ ድሬዳዋ የፍቅር እንዲሁም የአብሮነት ተምሳሌት ከተማ መሆኗን የተገለፀ ሲሆን፤ የዛሬው የአፍጢር ፕሮግራምም በክርስትና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች አስተባባሪነት መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።
ከዚህ በተጨማሪም ት/ቤቱ በድልጮራ ሆስፒታል ለሚገኙ ታካሚዎችና አስታማሚዎች የአፍጢር ግብአቶች ድጋፍ እንዳደረገ ተገልጿል።
በአጠቃላይም የዛሬው ፕሮግራም በተማሪዎች መካከል ያለውን የእርስ በእርስ ቅርበት ለመጨመር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል።
በአፍጢር መርሀ ግብሩ ሲያስተባብሩ ያነጋገርናቸው የክርስትና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞችም የረመዳን የፆም ወር የድሬዳዋ አብሮነት በይበልጥ የሚጎላበት መሆኑን ተናግረው፤ በቀጣይም እንደነዚህ አይነት ፕሮግራሞች ላይ በማስተባበር ከእህት ወንድሞቻችን ጎን ለመቆም ዝግጁ ነን ሲሉ ጠቁመዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ሰላም አበበ


